በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“መንበረ ጴጥሮስ አቋቋምን” ያሉ የኦሮምያ አቡኖች እንደታሰሩ ተነገረ


“መንበረ ጴጥሮስ አቋቋምን” ያሉ የኦሮምያ አቡኖች እንደታሰሩ ተነገረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:22 0:00

“የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስትያን መንበረ ጴጥሮስ” ሲሉ የሰየሙትን ሲኖዶስ ማቋቋማቸውን ይፋ ካደረጉ የሃይማኖት አባቶች መካከል ሦስቱ ትላንት፤ ማክሰኞ መታሠራቸውን የእንቅስቃሴው አስተባባሪዎች ገልፀዋል።

አቡኖቹ የታሠሩት መግለጫውን ከሰጡ በኋላ ሸገር ከተማ አስተዳደር በሚገኘው ቢሯቸው ውስጥ እንዳሉ መሆኑን ከ“መንበር” ምሥረታው አስተባባሪዎች አንዱ መሆናቸውን ለቪኦኤ የተናገሩት ዲያቆን አክሊሉ ዓለሙ ገልፀዋል።

ስለሁኔታው ከሸገር ከተማ አስተዳደርና ከፖሊስ መምሪያው ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ባለፈው ዓመት ተቀስቅሶ የነበረ ተመሳሳይ ውዝግብ በኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስትያንና ኦሮምያ ውስጥ በነበረው እንቅስቃሴ መሪዎች መካከል ውይይት ተካሂዶ መቋጨቱ በወቅቱ ተዘግቦ ነበር።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡

XS
SM
MD
LG