በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ የጅቡቲ የመጠጥ ውኃ አቅርቦቷን በአምስት ዕጥፍ ልታሳድግ ነው

please wait

No media source currently available

0:00 0:04:24 0:00

ኢትዮጵያ ለጅቡቲ በየዕለቱ የምታቀርበውን 20ሺሕ ሜትር ኩብ የመጠጥ ውኃ መጠን፣ ወደ 100ሺሕ ሜትር ኩብ ለማሳደግ እንደወሰነች ተገለጸ፡፡

የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ሀብታሙ ኢተፋ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ ለዚህ ውሳኔ አተገባበር ይጠቅማሉ የተባሉ ሥራዎች በመከናወን ላይ እንደኾኑ ተናግረዋል፡፡

ከመጠጥ ውኃ በተጨማሪ፣ ኢትዮጵያ ለጎረቤቶቿ የምታጋራቸው ሀብቶች እንዳሉ የጠቆሙት ሚኒስትሩ፣ ይህም ቀጣናዊ ትስስርን ለማጠናከር እና አብሮ ለማደግ ያስችላል፤ ብለዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡት፣ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ተመራማሪው ዶ/ር አቡሌ መሓሪ ደግሞ፣ ርምጃው ጠቃሚ እንደኾነ ገልጸው፣ ስምምነቱ ግን ጥንቃቄን እንደሚሻ አመልክተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG