በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻይናና ሩስያ ተጽዕኖ በአፍሪካ


የቻይናና ሩስያ ተጽዕኖ በአፍሪካ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:54 0:00

ቻያና እና ሩስያ እንደ ጸጥታው ምክር ቤት ባሉ ዓለማቀፋዊ ተቋማት የአፍሪካ ሃገራትን አቋም በመደገፍ በተደጋጋሚ መቆማቸው፣ በሃጉሪቱ ያላቸውን ተጽዕኖ ለማሳደግ እንዳገዛቸው ተገለጸ፡፡

በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግኑኝነት ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት ዶክተር ዮናስ አሽኔ፣ “የአፍሪካ ሃገራት ተለዋዋጭ እየሆነ በመጣው ዓለም አቀፋዊ ስርዓት ተስበው ለአንዱ አካል የመወገን አካሄድን በመከተል ብሄራዊ ጥቅማቸውን እንዳይጎዱ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል” ሲሉ መክረዋል፡፡

በስልታዊ እና ዓለም አቀፍ ጥናት ማዕከል የአፍሪካ ፕሮግራም ከፍተኛ አማካሪ ካሜሮን ሁድሰን በዩናይትድ ስቴትስ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ፣ የአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴ ቀርበው በሰጡት የምስክርነት ቃል፣ ሩስያ በአህጉሪቱ ህዝብ ውስጥ ያሉ ጸረ ምዕራብያውያን ስሜቶችን በማጉላት ብሄራዊ ጥቅሟን ለማስከበር ትሰራለች ሲሉ ተደምጠዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡

XS
SM
MD
LG