የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በቅርቡ ያወጣውና በሥራ ላይ ያዋለው ደንብ ቁጥር 4/2016፣ ከሕገመንግስቱ ጋራ ስለሚቃረን እና ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ስለሚዳርግ፣ በሕገመንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ እንዲሻር መጠየቁን፣ “ሂዩማን ራይትስ ፈርስት” የተባለ፣ ኢትዮጵያዊ የመብቶች ተሟጋች ድርጅት አስታወቀ፡፡
የድርጅቱ ዳይሬክተር አቶ ተስፋአለም በርኸ ለአሜሪከ ድምፅ በሰጡት አስተያየት፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ያወጣው ይኸው ደንብ፣ በፕሪቶርያው ስምምነት ህጋዊነቱን አጥቶ በፈረሰው ክልላዊ ምክር ቤት የወጡት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆች፣ በስራ ላይ እንዲቀጥሉ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ ከትግራይ ክልል ፍትህ ቢሮ አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡