በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ የግብፅን እና የአረብ ሊግን አቋም ተቃወመች


ኢትዮጵያ የግብፅን እና የአረብ ሊግን አቋም ተቃወመች
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:07 0:00

በኢትዮጵያ እና በሶማሊላንድ መካከል፣ ታኅሣሥ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. የተፈረመውን የመግባቢያ ሰነድ ተከትሎ ግብፅን እና የአረብ ሊግን ያራመዱትን አቋም ኢትዮጵያ ተቃወመች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒቴር ቃል አቀባይ መለስ ዓለም፣ የአረብ ሊግን መግለጫ “ለአፍሪካውያን ንቀት ነው” ሲሉ አጣጥለውታል።

የአረብ ሊግ የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ የሶማሊያን ሉዓላዊነት ይጎዳል ያለውን ስምምነት ውድቅ በማድረግ ሀገሪቱን የሚደግፍ መግለጫ አውጥቷል፡፡

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ ደግሞ፣ “ኢትዮጵያ የቀጣናው አለመረጋጋት ምንጭ ሆናለች “ ማለታቸውን መስሪያ ቤታቸው ገልጿል፡፡

አስተያየታቸውን “ቧልት” ነው ያሉት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም፣ የሊጉን መግለጫም “ተቀባይነት የለውም” ሲሉ በጽኑ ኮንነዋል፡፡

ድርጊቱ “በአፍሪካ ጉዳይ ላይ ጣልቃ የመግባት” ርምጃ እንደሆነም ገልጸውታል፡፡ ኢትዮጵያ በካምፓላው የኢጋድ አስቸኳይ የመሪዎች ስብሰባ ላይ የማትሳተፈው፣ “ግብዣው የቀረበበት ጊዜ አጭር በመሆኑ” እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG