በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማይክ ሃመር በኡጋንዳና ኢትዮጵያ ጉብኝት ያደርጋሉ


አምባሳደር ማይክ ሃመር (ፎቶ ፋይል ኤፒ ነሀሴ 21፣ 2023)
አምባሳደር ማይክ ሃመር (ፎቶ ፋይል ኤፒ ነሀሴ 21፣ 2023)

በምሥራቅ አፍሪካ የአሜሪካ ልዩ ልዑክ የሆኑት አምባሳደር ማይክ ሃመር ዛሬ በኡጋንዳ እንደሚከፈት በሚጠበቀው የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ወደ ስፍራው ማቅናታቸው ታውቋል። ከስብሰባው አጀንዳዎች አንዱ እንደሚሆን የሚጠበቀው ኢትዮጵያ እና ራስ ገዟ ሶማሊላንድ በቅርቡ የባሕር በርን በተመለከተ የፈረሙትን የመግባቢያ ሰነድ ተከትሎ የተፈጠረው ውጥረት እንደሆነ ታውቋል። ኢትዮጵያ በስብሰባው እንደማሳተፍ የኢትዮጵያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዛሬ አስታውቀዋል።

የኢጋድን ተነሳሽነት በመልካም እንደምትቀበለው የገለጸው የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ም/ቤት በበኩሉ፣ በእ.አ.አ 1960 የተወሰነውን የሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ድንበር፣ ሉአላዊነት እና የግዛት አንድነት እውቅና እንደሚሰጥ አስታውቋል።

ማይክ ሃመር በኢትዮጵያ ቆይታቸው፣ የሱዳንንም ሆነ ሌሎች የቀጠናው ጉዳዮች በተመለከተ ከአፍሪካ ኅብረት ባለሥልጣናት ጋር እንደሚነጋገሩ ሲጠበቅ፣ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር በሚኖራቸው ውይይት ደግሞ፣ የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ለማስቆም የተደረሰውን ስምምነት አፈጻጸም እንዲሁም በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል የሚታዩት ግጭቶች በሰላም በሚፈቱበት ጉዳይ ላይ እንደሚነጋገሩ ከአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG