በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ለውጪ ባንኮች ፈቃድ ልትሰጥ ነው


ፎቶ ፋይል፣ ሮይተርስ (ሐምሌ 31፣ 2019)
ፎቶ ፋይል፣ ሮይተርስ (ሐምሌ 31፣ 2019)

ኢትዮጵያ የውጪ ባንኮች በአገር ውስጥ የባንክ አገልግሎት መሳተፍ እንዲችሉ ፈቃድ መስጠት እንደምትጀምር ተቆጣጣሪው ባለሥልጣን አስታውቋል።

ተቆጣጣሪ አካል የሆነው የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባልሥልጣን ፈቃድ መስጠት እንዲጀምር የፍትህ ሚኒስቴር በዚህ ሳምንት ትዕዛዝ ማስተላለፉን የባለሥልጣኑ ኃላፊ የሆኑትን አቶ ብሩክ ታዬን ጠቅሶ የሮይተርስ ዜና ወኪል ዘግቧል።

ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋን ለውጪ መዋዕለ ነዋይ ክፍት ለማድረግ በመወሰኗ፣ እንደ ሳፋሪኮም ያሉ የቴሌፎን ኮባንያዎች በአገር ውስጥ ገበያ ተሳታፊ እንዲሆኑ አስችሏል። ነገር ግን፣ ተገማች ያልሆነው የቁጥጥር ሁኔታ፣ የፀጥታ መደፍረስ እና አጠቃላይ ኢኮኖሚው አለመረጋጋት በኩባንያዎቹ ሥራ ላይ ችግር ፈጥረዋል ሲሉ ተንታኞች በመናገር ላይ ናቸው።

በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የኢንቨስትመንት ባንኮች እንደሌሉ የጠቆመው ሪፖርቱ፣ ያሉት የንግድ ባንኮች በሚጠይቁት ከፍተኛ መያዥያ ምክንያት ብድሮችን ማግኘት አስቸጋሪ ነው ብሏል።

የገንዘብ ካፒታል ፍላጎት ከፍተኛ ነው ያሉት አቶ ብሩክ፣ ተበዳሪዎች 25 በመቶ ወለድ እና 70 በመቶ ደግሞ መያዥያ መጠየቃቸው፣ በኢትዮጵያ ካፒታልን ለማሳደግ እንቅፋት ሆኗል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ እጥረት እንዳለባት ያመለከተው ሪፖርቱ፣ ላለባት የ1 ቢሊዮን ዶላር ዓለም አቀፍ ቦንድ ክፍያ፣ ባለፈው ወር የነበረባትን የ 33 ሚሊዮን ዶላር ክፍያ ሳትፈጽም መቅረቷን አስታውሷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG