በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የራድዮ እና ቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ እና አቅራቢ አስፋው መሸሻ ሽኝት


የራድዮ እና ቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ እና አቅራቢ አስፋው መሸሻ ሽኝት
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:01 0:00

የራድዮ እና ቴሌቭዥን ፕሮግራም አዘጋጅ እና አቅራቢው አስፋው መሸሻ፣ በሕክምና ሲረዳ በቆየበት በዚኽ በዋሽንግተን ዲሲ፣ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ ጥር 4 ቀን 2016 ዓ.ም. ሕይወቱ አልፏል፡፡ አስፋውን በቅርበት የሚያውቁት ጓደኞቹ እና የሥራ ባልደረቦቹ፥ ሞያውን ወዳድነቱን፣ ተግባቢነቱንና ሰው አክባሪነቱን አብዝተው ይመሰክሩለታል፡፡

ታላቅ ወንድሙ አቶ በለጠ መሽሻም፣ አስፋው ከእርሳቸው ጋራ አብሮ ያደገና ከቤተሰቡም መሀከል አብዝተው የሚወዱት ወንድማቸው እንደነበረ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

በሠራባቸው የራድዮ እና የቴሌቭዥን የመዝናኛ ዝግጅቶች ተወዳጅነትን ያተረፈው አስፋው መሸሻ፣ በጥቅምት ወር 2016 ዓ.ም. በገጠመው የጤና መታወክ፣ በሀገር ውስጥ እና በአሜሪካ በሕክምና ሲረዳ ቢቆይም ሊሻለው ባለመቻሉ፣ በ57 ዓመት ዕድሜው ሕይወቱ አልፏል፡፡

ቤተሰቦቹን፣ የሥራ ባልደረቦቹንና ወዳጆቹን አነጋግረናል፡፡

XS
SM
MD
LG