የቱርክ መንግሥት፣ ትግራይ ክልል የሚገኘውን የአል-ነጃሺን መስጅድን ለማደስ መጠየቁን፣ የቅርሥ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ።
መነሻውን በትግራይ ክልል ባደረገው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት፣ መስጅዱ ጉዳት ደርሶበት እንደነበር ያስታወሱት የተቋሙ ዋና ዲሬክተር አቶ አበባው አያሌው፣ የቱርክ መንግሥት መስጅዱን መልሶ ለመጠገን መጠየቁንና በእድሳቱ ዙሪያም ጥናት እንደሚደረግ አመልክተዋል።
በጦርነቱ ትግራይ ክልል በሚገኙ ቅርሶች ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን ለማወቅም ተቋማቸው ጥናት ማካሔድ መጀመሩን ሓላፊው ጨምረው ገልፀዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡