በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሳንፍራንሲስኮን የጃዝ መንደር ዳግም ያነቁት ትውልደ-ኢትዮጵያዊ ሲታወሱ


ይወታቸውን የቀየረውን እና በከተማዋ ታሪክ ውስጥ ዛሬም በጉልህ የሚያስጠራቸውን ምዕራፍ የጀመሩት በ1986 የአውሮፓዊያኑ ዘመን ራሴላስ የተባለውን የጃዝ ክለብ በከፈቱ ማግስት ነበር ።
ይወታቸውን የቀየረውን እና በከተማዋ ታሪክ ውስጥ ዛሬም በጉልህ የሚያስጠራቸውን ምዕራፍ የጀመሩት በ1986 የአውሮፓዊያኑ ዘመን ራሴላስ የተባለውን የጃዝ ክለብ በከፈቱ ማግስት ነበር ።

ከሰሞኑ የሳንፍራንሲኮ ከተማ ትልቁ የህግ አወጪ ተቋም ፣ ለአንድ ትውልደ-ኢትዮጵያዊ የማስታወሻ አፍታ አስተናግዷል። ትውልደ- ኢትዮጵያዊው በከተማ ውስጥ የጃዝ ሙዚቃ ባህል ዳግም እንዲያንሰራራ ያገዙ ፣በተለያዩ ሰብዓዊ ተግባራት የከተማው ነዋሪ የደገፉ ስለ መሆናቸው በወቅቱ ተወስቷል። እኒህ ሰው አጎናፍር ሽፈራው ይባላሉ ። የከተማው ነዋሪዎች ደጋግመው በበጎ የሚያነሷቸውን ፣በቅርቡ በሞት የተለዩትን ሰው ታሪክ ሀብታሙ ስዩም ያስቃኘናል ።

በአውሮፓዊያኑ ታህሳስ ወር መጀመሪያ ላይ ፣በሰሜን ካሊፎርኒያ የምትገኘው የሳንፍራንሲስኮ ከተማ ህግ አውጪዎች፣ በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ አንድ ትውልደ-ኢትዮጵያዊን ዘክረዋል ። እሳቸው በከተማዋ ውስጥ በነበራቸው ወደ 40 ዓመታት የተጠጋ ዘርፈ ብዙ አበርክቶት በእጅጉ ይታወቃሉ ። ለዚያም ነው በእልፈታቸው ማግስት የከተማው ህግ አውጪዎችም ሆነ ከእሳቸው መልካም ስራ ያተረፉ ግለሰቦች ጥልቅ ሀዘናቸውን ለመግለጽ ያላመነቱት ። ትውልደ-ኢትዮጵያዊው አጎናፍር ሽፈራው ይባላሉ ።

አቶ አጎናፍር እና ሳንፍራንሲስኮ የተዋወቁት በአውሮፓዊያኑ 1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ ነው ። በሳንፍራንሲስኮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ለመከታተል ወደ ስፍራው የቀኑት ወጣቱ አጎናፍር ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካዊ ለውጥ እንዲፈጠር በውጭ ሀገራት ሲታገሉ ከነበሩት መካከል አንዱ ለመሆን ጊዜ አልፈጀባቸውም ።

የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መንግስት ተወግዶ የደርግ ዘመነ መንግስት በትረ-ስልጣኑን በጨበጠ ማግስት አቶ አጎናፍር ከፖለቲካዊ ትግሉ ባሻገር ወደ ሌላው የህይወታቸው ምዕራፍ ተሻገሩ ። ቀድመው በተመረቁበት የአስተዳደር ትምህርት ዘርፍ በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ ለ10 ዓመታት ያህል ካገለገሉ በኃላ የህንጻ መሳሪያዎች መደብር በመክፈት የንግዱን ዓለም ተቀላቅለዋል ። ህይወታቸውን የቀየረውን እና በከተማዋ ታሪክ ውስጥ ዛሬም በጉልህ የሚያስጠራቸውን ምዕራፍ የጀመሩት በ1986 የአውሮፓዊያኑ ዘመን ራሴላስ የተባለውን የጃዝ ክለብ በከፈቱ ማግስት ነበር ።

ራሴላስ ጃዝ ክለብ በከተማዋ ነዋሪ ዘንድን የመዝናኛ ስፍራ ብቻ አልነበረም ። ክለቡ የሚገኝበት ፊሊሞር ቀጠና በ1950ዎቹ እና 60ዎቹ ድንቅ ጥቁር የጃዝ ሙዚቃ ተጫዎቾች ገነውበት ነበር ። ከተማዋ በቀጣይ ዓመታት የዘረጋችው አወዛጋቢ የግንባታ መርሐ-ግብር ግን የቀጠናውን ድምቀት አወየበው ። የራሴላስ ጃዝ ክለብ ታዲያ የቀደመውን የጃዝ ታሪክ ያደሰ እና የተዳከመውን የጃዝ ባህል ያነቃቃ የኪነት እና መዝናኛ ስፍራ እንደነበረ ይወሳል ። ክለቡ ችሎታው ኖሯቸው ዕድሉን ለተነፈጉ ጥቁር አሜሪካዊያን የፈጠረውን መልካም ዕድል በህልፈታቸው ማግስት በዕድሉ ተጠቃሚ የሆኑ የሙዚቃ ሰዎች አስተጋብተውታል ።


ሀብታሙ ስዩም ባለ ትዳር እና የአንዲት ሴት ልጅ አባት የነበሩትን የሳንፍራንሲሶኮን ጃዝ መንደር አንቂ ታሪክ በአጭሩ ያስቃኘናል ።

የሳንፍራንሲስኮን የጃዝ መንደር ዳግም ያነቁት ትውልደ-ኢትዮጵያዊ ሲታወሱ
please wait
  • Auto
  • 240p
  • 360p
  • 480p
  • 720p
  • 1080p

No media source currently available

0:00 13:38 0:00
  • Auto
  • 240p
  • 360p
  • 480p
  • 720p
  • 1080p

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG