በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በካታር ኢትዮጵያን የሚያስተዋውቀው ሠዓሊ  


በካታር ኢትዮጵያን የሚያስተዋውቀው ሠዓሊ  
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:12 0:00

በካታር ኢትዮጵያን የሚያስተዋውቀው ሠዓሊ  

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አለ ፈለገ ሰላም የሥነጥበብ ትምህርት ቤት የተመረቀው ሠዓሊ ተሰማ ተምትሜ ያለፉት 15 ዓመታትን ነዋሪነቱን በመካከለኛው ምስራቅ ካታር አድርጓል። ሠዓሊ ተሰማ በኢትዮጵያ እና በተለያዩ ሀገራቶች ተዟዙሮ ስራዎቹን ያቀረበ ሲሆን በዋናነትም በሰው ቁመት ልክ የሰራው የቡና ቅርጽ፤ በካታር የቅርስ ማዕከል በሚካሄድ ትዕይንት አካል በመሆን እስከ መጪው መጋቢት ድረስ ለዕይታ ክፍት ነው።

ቅርጹ በነሃስ በድጋሚ ተሰርቶ በካታር በተመረጠ ጎዳና ላይ እንዲቀመጥ እንቅስቃሴ መጀመሩንም አርቲስቱ ለአሜሪካ ድምጽ አስታውቋል።

“የሥዕል ስራዎቼ ደግነት እና ሀገር ማስተዋወቅ እንዲሁም ዲፕሎማሲን ዓላማ ያደረጉ ናቸው” የሚለው አርቲስቱ፤ በዋናነት የሙሉ ጊዜ መተዳደሪያው የአቪዬሽን ስራ ነው። ሠዓሊ ተሰማ በቅርቡ ስቱዲዮውን ወደ ጋለሪነት ለማሳደግ ዓልሞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ለአሜሪካ ድምጽ አጋርቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG