በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሐማስ የታገቱት እንዲለቀቁ የሚጠይቅ ሰልፍ በቴል አቪቭ ተካሄደ


በቴል አቪቭ “የታጋቾች አደባባይ” ከተካሄደው ሰልፍ በከፊል (ፎቶ ኤፒ ጥር. 13, 2024)
በቴል አቪቭ “የታጋቾች አደባባይ” ከተካሄደው ሰልፍ በከፊል (ፎቶ ኤፒ ጥር. 13, 2024)

በሺሕ የሚቆጠሩ እስራኤላውያን ከትናንት ምሽት ጀምሮ ለ24 ሰዓታት የሚቆይ ሰልፍ በቴል አቪቭ በማድረግ ላይ ናቸው። ሰልፈኞቹ የተሰባሰቡት የእስራኤል መንግስት በሐማስ የታገቱ እስራኤላውያንን እንዲያስለቀቅ ጥሪ ለማድረግ ነው።

ታጋቾቹ እነደፈረንጆቹ አቆጣጠር ጥር 7 ቀን በሐማስ ከተወሰዱ አንድ መቶኛ ቀናቸውን አስቆጥረዋል።

የታጋቾቹን ፎቶግራፍ በማያዝ “የታጋቾች አደባባይ” ብለው በሚጠሩትና ከእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ፊት ለፊት በሚገኘው ሥፍራ የተሰባሰቡት ሰልፈኞች፣ በሐማስ ቁጥጥር ሥር ያሉ ውዶቻቸው ሊደርስባቸው ስለሚችለው ስቃይ እና እንግልት ተናግረዋል።

በሰልፉ ላይ ንግግር ያደረጉት የአሜሪካው አምባሳደር ጄከብ ሊው፣ የፕሬዝደንት ባይደን አስተዳደር የቀሩት ታጋቾችን በሙሉ ለማስለቀቅ ቁርጠኛ ነው ብለዋል።

የፈረንሣዩ ፕሬዝደንት አማኑኤል ማክሮን በቪዲዮ በላኩት መልዕክት፣ በሐማስ ቁጥጥር ሥር ያሉት ሁለት ፈረንሣውያንም ሆነ የተቀሩት ታጋቾችን ለማስለቀቅ አገራቸው አስፈላጊውን ሁሉ ታደርጋለች ብለዋል። “ፈረንሣይ ልጆቿን አትጥልም” ሲሉም ተደምጠዋል። ታጋቾቹን ለማስለቀቅ ይደረግ የነበረው ድርድር እንዲቀጥልም ጥሪ አድርገዋል።

ባለፈው ኅዳር ከሐማስ ጋር በተደረገው ጊዜያዊ ተኩስ ማቆም፣ ከ100 በላይ የሚሆኑ ታጋቾች ሲለቀቁ፣ 132 የሚሆኑት አሁንም በሐማስ እጅ ይገኛሉ።

የታጋቾቹ ቤተሰቦች፤ የእገታውን 100ኛ ቀን ምክንያት በማድረግ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ነታንያሁ መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት እና ቅድሚያ እንዲሰጠው ጠይቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG