በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በታይዋን ምርጫ የዲሞክራቲክ ተራማጅ ፓርቲው እጩ አሸነፉ


በታይዋን የዲሞክራቲክ ተራማጅ ፓርቲው (ዲፒፒ) ፓርቲ ደጋፊዎች ደስታቸውን ሲገልጹ (ፎቶ ኤፒ ጥር 13, 2024)
በታይዋን የዲሞክራቲክ ተራማጅ ፓርቲው (ዲፒፒ) ፓርቲ ደጋፊዎች ደስታቸውን ሲገልጹ (ፎቶ ኤፒ ጥር 13, 2024)

በታይዋን ምርጫ የዲሞክራቲክ ተራማጅ ፓርቲው (ዲፒፒ) እጩ እና ምክትል ፕሬዝደንት የነበሩት ላይ ቺንግ-ተ ፕሬዝደንታዊ ምርጫውን ማሸነፋቸው ይፋ ሆኗል።

ታይዋናውያን የቻይናን ዛቻ ችላ በማለት ትናንት ፕሬዝደንታቸውን ለመምረጥ ድምጽ ሲሰጡ ውለዋል።

የተለያዩ የዓለም አገራት እና መንግስታት ለአዲሱ ፕሬዝደንት የደስታ መግለጫ መልዕክት መላካቸው ቻይናን እጅግ ያስቆጣት ጉዳይ ሆኗል።

ቻይና፣ ደሴቲቱን ታይዋን እንደ ግዛቷ የምትቆጥራት ሲሆን፣ አስፈላጊ ከሆነ በኃይል እንደምትቀላቅላት ስትዝት ከርማለች፡፡

የ ላይ ቺንግ-ተ ምርጫውን ማሸነፍ ሕዝቡ በዴሴቲቱ ጉዳይ ላይ ያለውን አጠቃላይ አስተያየት አያሳይም ሲል በቻይና የታይዋን ጉዳዮች ቢሮ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በሁለቱ መካከል ያለውን ሁኔታም እንደማይቀረው ቢሮው በመግለጫው አመልክቷል።

የቅዳሜውን ምርጫ በተመለከተ አስተያየት እንዲሰጡ የተጠየቁት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን፣ “የታይዋንን ነጻነት አንደግፍም“ ነገር ግን ማንኛውም አገር በምርጫው ላይ ጣልቃ ቢገባ ተቀባይነት አይኖረውም ብለዋል።

የእንግሊዝ የጃፓን እና የሌሎችም አገራት ለታይዋኑ አዲስ ፕሬዝደንት የደስታ መግለጫ ሲልኩ፣ የሩሲያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ባወጡት መግለጫ፣ ሞስኮ ታይዋንን እንደ ቻይና አካል አድርጋ መመልከቷን ትቀጥላለች ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG