በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ አህጉር ገናና የእግር ኳስ ፍልሚያ ዛሬ ይጀመራል


አዘጋጇ ኮትዲዮቫር ከጊኒ ቢሳው ጋር የምትገናኝበት የመክፈቻ ጨዋታ ጨዋታ ትኬቶች ተሸጠው ያለቁ ሲሆን ፣ ጨዋታው በዓለም ላይ በሚገኙ 170 ሀገራት እንደሚተላለፍ አሰናጁ አካል በኦፊሳሊያዊ ድረ-ገጹ ላይ አስታውቋል ።
አዘጋጇ ኮትዲዮቫር ከጊኒ ቢሳው ጋር የምትገናኝበት የመክፈቻ ጨዋታ ጨዋታ ትኬቶች ተሸጠው ያለቁ ሲሆን ፣ ጨዋታው በዓለም ላይ በሚገኙ 170 ሀገራት እንደሚተላለፍ አሰናጁ አካል በኦፊሳሊያዊ ድረ-ገጹ ላይ አስታውቋል ።

አፍሪካዊያን የእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪያን በጉጉት የሚጠብቁት የአህጉሪቱ ግዙፍ ውድድር
በዛሬው ዕለት ከጥቂት ሰዓታት በኃላ ይጀመራል ።

የዘንድሮው አዘጋጅ ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ኮትዲቮር ስትሆን ፣ የመክፈቻው ዝግጅት በ"አላሳን ዋታራ ስታዲየም" ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል ። አዘጋጇ ኮትዲዮቫር ከጊኒ ቢሳው ጋር የምትገናኝበት የመክፈቻ ጨዋታ ትኬቶች ተሸጠው ያለቁ ሲሆን ፣ ጨዋታው በዓለም ላይ በሚገኙ 170 ሀገራት እንደሚተላለፍ አሰናጁ አካል በኦፊሳሊያዊ ድረ-ገጹ ላይ አስታውቋል ።

ለ34ኛ ጊዜ በሚደረገው የአፍሪካ የእግር ኳስ ፈርጦች የሚገናኙበት የስፖርት አውድማ ላይ 24 ሀገራት ዋንጫውን ለመሳም ይፋለማሉ ።


በአውሮፓዊያኑ 1957 ዓመተ ምህረት ሱዳን፣ካርቱም ውስጥ በሶስት ሀገራት ማለትም ፣ በሱዳን ፣ በግብጽ እና ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ተሳትፎ የጀመረው የአፍሪካ ዋንጫ የአህጉሪቱን የስፖርት አፍቃሪያን ቀለብ እንደገዛ ዓመታትን ተሻግሯል ። በውድድሩ ታሪክ ግብጽ ለ7 ጊዜ ያህል ዋንጫውን በማንሳት ክብረወሰን ይዛለች ።


ከዚህ ቀደም በአውሮፓዊያኑ 1984 የአፍሪካ ዋንጫን የማዘጋጀት ዕድል ያገኘችው ኮትዲዮቫር ፣ በ1992 የአውሮፓዊያኑ ዘመን የአፍሪካን ዋንጫ ለማሸነፍ በቅታለች ። አዲስ የድል ታሪክ ለማስመዝገብ ፣ ሞሮኮ ፣ ሴኔጋል ፣ ግብጽ እና ናይጄሪያን ከመሰሉ የአህጉሩ የእግር ኳስ ገናናዎች ጋር የጋለ ፉክክር ይጠብቃታል ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG