በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፌዴራል መንግሥቱ ለኢንዱስትሪ ዘርፉ ድጋፍ እንዲያደርግ የትግራይ ክልል የኢንዱስትሪ ቢሮ ጠየቀ


ፌዴራል መንግሥቱ ለኢንዱስትሪ ዘርፉ ድጋፍ እንዲያደርግ የትግራይ ክልል የኢንዱስትሪ ቢሮ ጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:03 0:00

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የተጎዳው የትግራይ ክልል የኢንዱስትሪ ዘርፍን ለማነቃቃትና የወደሙትን ፋብሪካዎች መልሶ ለመገንባት፣ የፌዴራሉ መንግሥት፣ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንዲያደርግ፣ የክልሉ የኢንዱስትሪ ቢሮ ጠየቀ፡፡ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ መሐሪ ገብረ ሚካኤል ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ ከጦርነቱ በፊት በትግራይ የነበሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች አብዛኞቹ በጦርነቱ መጎዳታቸውን ተናግረዋል፡፡

የፕሪቶርያውን ሥምምነት ተከትሎ፣ በክልሉ ሰላም ቢፈጠርም፣ የኢንዱስትሪ ዘርፉን መልሶ ለመገንባት የፌዴራሉ መንግሥት በቂ ድጋፍ እያደረገ አይደለም ብለዋል፡፡ ዘርፉን በማነቃቃት በክልሉ ያለውን ድህነት እና ሥራ አጥነት ለመቀነስ እንዲቻልም፣ መንግሥት ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንዲያደርግ አቶ መሐሪ ጠይቀዋል፡፡

ስለ ጉዳዩ ከአንዱስትሪ ሚኒስቴር ምላሽ ለማግኘት የተደረገው ጥረት ለግዜው አልተሳካም፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡

XS
SM
MD
LG