በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቅርሶችን ከጥፋት ለማዳን የባለድርሻ አካላት ውይይት እንዲደረግ ተጠየቀ


ቅርሶችን ከጥፋት ለማዳን የባለድርሻ አካላት ውይይት እንዲደረግ ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:36 0:00

በኢትዮጵያ የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶችን ከጥፋት ለማዳን፣ የባለድርሻ አካላት ውይይት እንዲደረግ የኢትዮጵያ የሥነ ህንጻ ባለሙያዎች ማኅበር ጠየቀ፡፡ የተቋሙ ፕሬዚዳንት አቶ ሀብታሙ ጌታቸው፣ በአዲስ አበባ የሚገኘውና በተለምዶ ሎምባርዲያ ተብሎ የሚጠራው የሼህ አሕመድ ሳላህ ህንፃ እንዲፈርስ መደረጉን መነሻ አድርገው ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለመጠይቅ፣ የልማት ፍላጎትና የቅርስ ጥበቃን ለማስታረቅ፣ ውይይት መደረግ አለበት ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኅበር በበኩሉ፣ የሎምባርዲያ ታሪካዊ ህንፃ እንዳይፈርስ በፍርድ ቤት ሲከራከር መቆየቱን አስታውቋል፡፡ በመጨረሻ ግን፣ ህንፃው ከቅርስነት ዝርዝር ተሰርዟል ተብሎ እንዲፈርስ እንደተወሰነ የማኅበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ማቆያ ማሞ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡ የቅርሶች ደህንነት አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንዳለም አክለዋል፡፡ የኢትዮጵያ የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን በበኩሉ “ህንፃው የቅርስነት መመዘኛ አላሟላም”ብሏል፡፡

XS
SM
MD
LG