በእስራኤል እና በሐማስ መካከል በሚካሄደው ጦርነት ምክንያት በቀጠናው ያለው ውጥረት እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ከተለያዩ የአረብ መሪዎች ጋር ተገናኝተዋል። በሌላ በኩል እስራኤል ፍልስጤማውያን በግዳጅ ከጋዛ ውጪ እንዲሰፍሩ ባይደረግም ጦርነቱ ግን ይቀጥላል ስትል በግልፅ ተናግራለች።
በዚህ ዙሪያ የአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ ቬሮኒካ ባልደራስ ኤግሊሲያስ ያደረሰችንን ዘገባ ስመኝሽ የቆየ ወደ አማርኛ መልሳዋለች፡፡