በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ የዩክሬን ሚሳዬሎችን መጣሏን አስታወቀች


የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን

በጦርነቱ የሚደርስባት ጉዳት እያየለ ነው

የሩሲያ አየር መከላከያ ክራይሚያ ውስጥ ዛሬ ቅዳሜ ጧት በዩክሬን የሚመሩ ሚሳዬሎችን በመጥለፍ ማውደሙን አስታወቀ፡፡

በተጨማሪም የአየር መከላከያ ክፍሎች በክራይሚያ ባሕረ ገብ መሬት እና በጥቁር ባህር ምዕራባዊ ክፍል ላይ ትናንት ዓርብ ምሽቱን በፈጸሟቸው ተከታታይ ጥቃቶች ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መተው መጣላቸው ተዘግቧል።

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ በዚህ ዓመት በክራይሚያ ባሕረ ገብ መሬት እና በሩሲያ ድንበር ክልሎች ውስጥ ተጨማሪ ኢላማዎችን ለመምታት መዛታቸው በመጭው መጋቢት የሩሲያ ፕሬዚዳንት በመሆን እንደገና ለመመረጥ የሚያስቡት ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንን አስደንግጧቸው እንደነበር ተነግሯል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የብሪታንያ መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ቅዳሜ ኤክስ ላይ ባሰፈረው መረጃ ሩሲያ ዩክሬን ውስጥ በየቀኑ የሚደርስባት ጉዳት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸ በ300 ያህል ጨምሯል ብሏል፡፡

ጉዳቱ አሁን ባለው መጠን ከቀጠለ ሩሲያ በዓመቱ መጨረሻ "በዩክሬን ጦርነት ከግማሽ ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ሊሞቱና ሊቆስሉባት" ይችላሉ ሲል የሚኒስቴሩ መግለጫ አመልክቷል፡፡

የብሪታኒያው ሚኒስቴር በንጽጽር ባወጣው መረጃ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1979 እስከ 1989 ባለው ጊዜ አፍጋኒስታን ውስጥ 70,000 የሚሆኑ የሶቪየት ህብረት ተዋጊዎች ሰለባ ሆነዋል ብሏል።

በሌላም በኩል የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የበጀት ከፍተኛ ባለስልጣን ትናንት ዓርብ በሰጡት ከባድ ማስጠንቀቂያ አሜሪካ ለዩክሬን የምትሰጠውን እርዳታ ለማሟለት ህግ አውጭዎች የቀራቸው ጊዜ እያለቀ ነው ብለዋል፡፡

ለዩክሬን ድጋፍ የተጠቀየው በጀት በምክር ቤት ውስጥ ባለ የስደተኞች ጉዳይ የበጀት ድርድር እስካሁን እልባት ያልተሰጠው መሆኑ ተመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG