ዕውቁ የታይም መጽሔት በአየር ንብረት መዛባት ላይ ትኩረት ባደረገው ልዩ የመጀመሪያ ዕትሙ፥ በተለይ የከባቢ አየር ብክለትን ለመዋጋት በዓለም ዙሪያ በተያዘው ትግል “ዓይነተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ናቸው” በሚል ለመረጣቸው አንድ መቶ የተለያዩ ኩባንያዎች መሪዎች እና ሌሎች ታዋቀ ሰዎች በቅርቡ እውቅና የሰጠበትን ዝርዝር ይፋ አድርጓል።
ኢትዮጵያዊው ቅዱስ አስፋው ከፍተኛ የከባቢ ዓየር ብክለት የሚያከትሉ የፕላስቲክ ተረፈ ምርቶችን ዝቅተኛ የካርቦን ልቀት ወዳላቸው የግንባታ ግብአቶች በሚቀይረው እና በዋና ሥራ አስፈጻሚነት በሚመራው ኩባንያቸው እንቅስቃሴዎች ባሳየው የአቅኚነት ሥራው ታይም ‘መቶዎቹ’ ምርጦች ሲል ዕውቅና ካጎናጸፋቸው ውስጥ አንዱ ለመሆን በቅቷል።
ዝነኛይቱ አሜሪካዊት አቀንቃኝ ቢሊ ኤሊሽ፣ ያሁኑ የሮከፌለር የበጎ አድራጎት ተቋም ፕሬዝዳንት የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የተራድኦ ፕሮግራም አስተዳዳሪ ዶ/ር ራጂቭ ጄ ሻህ እና የማይክሮ ሶፍት ኩባንያው መስራቹ ቢሊየነር ቢል ጌትስም በተመሳሳይ መጽሔቱ ከመረጣቸው ውስጥ ይገኙበታል።
የዚህን ዘገባ ዝርዝር ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ፡፡