በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤል ጦር የተወሰኑ ኃይሎች ለስልጠና ከጋዛ ሊያስወጣ ነው


ፎቶ ፋይል፦ የእስራኤል ወታደሮች በጋዛ ሰርጥ
ፎቶ ፋይል፦ የእስራኤል ወታደሮች በጋዛ ሰርጥ

እስራኤል ከሐማስ ጋር ለምታደርገው ለወራት የሚቀጥል ጦርነት ለመዘጋጀት፣ ሰኞ እለት የተወሰኑ ወታድሮቿን ለእረፍት እና ለስልጠና ከጋዛ እንደምታስወጣ አስታውቃለች።

የጦሩ ቃል አቀባይ ሪር አድሚራል ዳንኤል ሀጋሪ ለጋዜጠኞች እንዳስታወቁት የተወሰኑ የተጠባባቂ ኃይል አባላት በዚህ ሳምንት ወደእስራኤል ይመለሳሉ። "ይህ እርምጃ በኢኮኖሚው ላይ ያለውን ጫና የሚያቀል ነው" ያሉት ሀጋሪ፣ "ውጊያው የሚቅጥል በመሆኑ ወታድሮቹ በመጪው አመት ለሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ጥንካሬያቸውን እንዲያሰባስቡ ይረዳቸዋል" ብለዋል።

እስራኤል በጋዛ በምታደርገው ወታደራዊ ዘመቻ ሲቪሎችን ለመጠበቅ፣ ዝቅተኛ ኃይል እንድትጠቀም ዋና አጋሯ ከሆነችው ዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ጫና እየተደረገባት ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በጋዛ ሰርጥ የሚገኙት የሐማስ ታጣቂዎች ሰኞ እለት ሮኬቶችን ወደ እስራኤል በመተኮሳቸው በእስራኤል የማስጠንቀቂያ ደወሎች ተደውለዋል። በጥቃቱ ምክንያት የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ ግን የተዘገበ ነገር የለም።

እስራኤል በበኩሏ ሰኞ እለት የመሬት ላይ ዘመቻዎችን እና የአየር ላይ ጥቃቶች ማድረስ የቀጠለች ሲሆን፣ ሐማስ በጥቅምት ሰባት ያደረሰውን ጥቃት የመራው ኮማንደር በጥቃቱ መገደሉን የእስራኤል መከላከያ ኃይል አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG