በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና 9 የጦር ባለስልጣናትን ከፓርላማዋ አባረረች


ባለፈው መጋቢት ተሹመው የነበሩት ሊ በይፋ በጥቅምት ወር ከስልጣን መነሳታቸው ቢነገርም ከነሐሴ ወር ጀምሮ ከህዝብ ዕይታ ርቀዋል ።
ባለፈው መጋቢት ተሹመው የነበሩት ሊ በይፋ በጥቅምት ወር ከስልጣን መነሳታቸው ቢነገርም ከነሐሴ ወር ጀምሮ ከህዝብ ዕይታ ርቀዋል ።

አዲስ የመከላከያ ሚኒስትር ሹመትን ተከትሎ ቻይና ባደረገችው ከፍተኛ ሹምሽር አራት የጦር ኃይሎች ስትራቴጂካዊ ሚሳኤል ክፍል ጄኔራሎችን ጨምሮ ዘጠኝ ወታደራዊ ባለስልጣናትን ከፓርላማዋ አባረረች።

የገዥው ኮሚኒስት ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ካደረገ በኋላ አርብ መገባደጃ ላይ በመንግስት የዜና ወኪል ዢንዋ ውሳኔው ይፋ ሆኗል ።ለባለሥልጣናቱ ከስልጣን መነሳታቸው ምንም አይነት ማብራሪያ አልተሰጠም።

የባለስልጣናቱ መነሳት ፣ የሀገሪቱ የጦር ሚኒስትር የነበሩት ሊ ሻንግፉ ከስልጣን ከተነሱ በኃላ ከተደረጉ ተከታታይ የጦር ኃይሉ የከፍተኛ አመራር የሽግሽግ ርምጃዎች መካከል አንዱ ነው።

ባለፈው መጋቢት ተሹመው የነበሩት ሊ በይፋ በጥቅምት ወር ከስልጣን መነሳታቸው ቢነገርም ከነሐሴ ወር ጀምሮ ከህዝብ ዕይታ ርቀዋል ። ያሉበት ስፍራም አይታወቅም ።አርብ እለት ቤጂንግ ዶንግ ጁን አዲስ የመከላከያ ሚኒስትር አድርጋ በመሾም ቁልፍ በሆነው እና ለወራት ክፍት ሆኖ በቆየው ቦታ ባልስልጣን ተክታለች ።

የቤጂንግን የኒውክሌር ጦር መሳሪያን የሚቆጣጠረው የቻይናው ሚስጥራዊ የሮኬት ሃይል አመራር በቀድሞው አለቃ ላይ የሙስና ምርመራ መደረጉን የመገናኛ ብዙሀን ይፋ ካደረጉ በኃላ ባሉት ቅርብ ጊዜያት ውስጥ ተከትሎ ለውጦች ታይቷል።

ከብሔራዊ ህዝባዊ ኮንግረስ የተባረሩት ዘጠኙ ባለስልጣናት ያልተመረጡ ተወካዮች ሆነው በፓርላማው ውስጥ ቆይተዋል።

የባለስልጣናቱ መባረር ፣ "ባለስልጣናቱ ምርመራ ተከፍቶባቸዋል " ፣ የሚለውን ግምት በማጉላት በጉዳዩ ላይ ሲሰራጩ የነበሩ ወሬዎችን እርግጥ መሆናቸውን ማሳየቱን በዩናይትድ ስቴትስ መሰረቱን ያደረገው ሲኖኢንሳይደር የተሰኘው በቻይና ፖለቲካ ላይ ያተኮረው ተቋም አስታውቋል ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG