በደቡብ አፍሪካ ኩዋዙሉ-ናታል ግዛት ውስጥ በምትገኝ ሌዲስሚዝ በተባለች ትንሽ ከተማ በደረሰ የጎርፍ አደጋ ከ12 በላይ ሰዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ባለስልጣናት ገለፁ።
የፖሊስ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ሮበርት ኔትሺንዳ “እ.ኤ.አ ከ ከአርብ ታህሳስ 29 ቀን 2023 አንስቶ በአጠቃላይ 21 አስከሬኖች ተገኝተዋል” ብለዋል።
ቃል አቀባዩ የጎርፍ አደጋው በከተማዋ የገና በዓል ዕለት በመከሰቱ ወደ 1,400 የሚጠጉ ቤቶችን መውደማቸው የጠቆሙ ሲሆን ቁጥራቸው ያልተረጋገጠ ሰዎች አሁንም እንደጠፉ በመሆናቸው የሟቾች አሃዝ ሊጨምር እንደሚችልም ተናግረዋል።
የነፍስ አድን እና የፍለጋ ቡድኖች አስከሬን ለማግኘት ወንዞችን ሲቃኙ ቆይተዋል በማለት ኔትሺንዳ ተናግረዋል። የፍለጋ ልዑኮቹ ቅዳሜና እሁድ በሙሉ እንደሚቀጥሉ ይጠበቃል።
መድረክ / ፎረም