በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን የቀድሞ ሰላም አስከባሪ አባላት “ስጋት ስላለብን ወደ ሌላ ሀገር እንዛወር” አሉ


በሱዳን የቀድሞ ሰላም አስከባሪ አባላት “ስጋት ስላለብን ወደ ሌላ ሀገር እንዛወር” አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:59 0:00

ሱዳንንና ደቡብ ሱዳንን በምታጨቃጭቀው በአቢዬ ግዛት፣ በሰላም ማስከበር ተልእኮ ላይ ተሰማርተው የነበሩና በሱዳን ጥገኝነት የጠየቁ 248 የትግራይ ተወላጅ የቀድሞ የመከላከያ አባላት፣ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር(UNHCR) ወደ ሌላ ሀገር እንዲያዛውራቸው ጠየቁ፡፡

በሱዳን የቀጠለው የእርስ በርስ ጦርነት፣ ስጋት ላይ እንደጣላቸው የተናገሩት የቀድሞ የመከላከያ አባላት፣ ደኅንነታቸው ወደሚጠበቅበት ሌላ ሀገር እንዲያዛውራቸው፣ ዓለም አቀፍ የስደተኞች ተቋሙን በደብዳቤ እንደጠየቁ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በስልክ ገልጸዋል፡፡

ስለ ጉዳዩ፣ የአሜሪካ ድምፅ የጠየቀው የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር በበኩሉ፣ ከስደተኞቹ ጥያቄው እንደቀረበለት ገልጾ፣ “ስጋታቸውን እንረዳለን፤ ኾኖም ስደተኞችን ወደ ሌላ የአፍሪካ ሀገር የማዛወር ሥልጣን የለንም፤” ሲል ምላሽ ሰጥቷል፡፡

በተመሳሳይ ዜና፣ በምሥራቅ ሱዳን፣ ኡምራኩባ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ስደተኞችም እንደዚኹ፣ የሱዳኑ ጦርነት እንዳሰጋቸው ገልጸው፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲደርስላቸው ተማፅነዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

XS
SM
MD
LG