በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ ግጭት የካፒታልንና ሠራተኞችን ነጻ ዝውውር በማወኩ “የአምራች ዘርፉ እየተፈተነ ነው”


በኢትዮጵያ ግጭት የካፒታልንና ሠራተኞችን ነጻ ዝውውር በማወኩ “የአምራች ዘርፉ እየተፈተነ ነው”
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:13 0:00

በኢትዮጵያ የሚታየው የጸጥታ ችግር፣ ለአምራች ኢንዱስትሪው ትልቅ ማነቆ እንደኾነ፣ የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም(UNDP) ጥናት አመለከተ፡፡

በጥናቱ ላይ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡት፣ የተቋሙ የኢኮኖሚ ባለሞያ አቶ ኀይሌ ክብረት፣ ከአምስት ዓመታት በላይ የዘለቀው ግጭት እና አለመረጋጋት፣ “የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ጎድቷል፤ የካፒታል እና የሠራተኞች ነጻ እንቅስቃሴ እንዳይኖርም አድርጓል፤” ይላሉ፡፡

የኢንዱስትሪ ዘርፉ፥ ከብድር አቅርቦት፣ ከፖሊሲ ርግጠኝነት አለመኖርና ከውጭ ምንዛሬ እጥረት ጋራ የተያያዙ ተግዳሮቶችም እንዳሉበት፣ ባለሞያው ገልጸዋል፡፡ ዘርፉ እንዲነቃቃም፣ ከመንግሥት በኩል አጠቃላይ ትኩረት እንደሚሻም፣ አክለው አመልክተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG