የአሜሪካው የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስትን፣ ትላንት ሰኞ፣ እስራኤልን በጎበኙበት ወቅት፣ አገራቸው ለአገሪቱ ያላትን የማይናወጥ ድጋፍ በድጋሚ አረጋግጠዋል።
በአንጻሩም፣ የፍልስጥኤማውያን ሲቪሎችን ደኅንነት መጠበቅ፣ “ከሞራልም ኾነ ከስልት አኳያ ግዴታ ነው፤” ያሉት የመከላከያ ሚኒስትሩ፣ ጦርነቱ ካበቃም በኋላ፣ “የኹለት አገራት ምሥረታ መፍትሔ” ላይ የመድረስ አስፈላጊነትን፣ አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።
የቪኦኤዋ ቬሮኒካ ባልዴራስ ኢግሌሲያስ ዝርዝሩን ልካለች፡፡ እንግዱ ወልዴ ወደ ዐማርኛ መልሳዋለች፡፡