• እስራኤል የሰላማውያኑን ሕይወት እንደትጠብቅ ጫና በዝቶበታል
እስራኤል በሐማስ ላይ የጀመረችውን ጦርነት በቀጠለችበት ወቅት፣ የክልሉን ጸጥታ ለማጠናከር ያለሙት የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን፣ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ተጉዘዋል።
እስራኤል በወታደራዊ ዘመቻዋ፣ ሰላማውያን ነዋሪዎችን እንዳታጠቃና እ.ኤ.አ. ጥቅምት 7 ቀን በሐማስ የሽብር ወረራ ታግተው የነበሩትን ኹሉ እንድታስለቅቅ ጫናው እየበረታባት ነው።
የቪኦኤዋ ዘጋቢ ቬሮኒካ ባልደራስ ኤግሊስያስ፣ ተከታዩን ዘገባለች፤ ደረጀ ደስታ ወደ ዐማርኛ መልሶታል፡፡