በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋምቤላ ክልል አበቦ ወረዳ አራት ሰዎች በታጣቂዎች እንደተገደሉ ተገለጸ


በጋምቤላ ክልል አበቦ ወረዳ አራት ሰዎች በታጣቂዎች እንደተገደሉ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:13 0:00

በጋምቤላ ክልል አኙዋክ ዞን በአቦቦ ወረዳ መንደር 17 ቀበሌ ውስጥ፣ ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ፣ ታጣቂዎች አደረሱት በተባለ ጥቃት፣ አራት ሰዎች እንደተገደሉ፣ ቤተሰቦቻቸው እና የዐይን እማኞች፣ በስልክ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

ወንድሟ፣ በታጣቂዎቹ በስለት ተወግቶ እንደተገደለ የገለጸች አንዲት ወጣት፣ በእርሷም ላይ ጉዳት ለማድረስ እንደሞከሩ ተናግራለች። ጥቃቱ “በማንነት ላይ ያተኮረ ነው፤” ሲሉም የሟች ቤተሰቦች ይወቅሳሉ።

የጋምቤላ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ሓላፊ ኡጁሉ ጊሎ፣ አራት ሰዎች በታጣቂዎች እንደተገደሉ አስታውቀው፣ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር ለማዋል፣ የጸጥታ ኀይሎች አሰሳ ላይ ናቸው፤ ብለዋል።

ኾኖም ድርጊቱ፣ “ማንነትን መሠረት ያደረገ አይደለም፤” ሲሉ፣ የኮምዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤቱ ሓላፊው አስተባብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG