በሰላም ዕጦት ምክንያት በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ የሀገራት የጉዞ እገዳዎች፣ ቱሪዝሙን እንደጎዳው በዘርፉ ላይ የሚሠሩ ባለሞያዎች ገለጹ፡፡
የአገሪቱ የቱሪስት መስሕቦች እና በዙሪያቸው የሚሠሩ ድርጅቶች፣ በጎብኝዎች ዕጦት እየተፈተኑ እንደኾነ፣ የጉዞ እና ጉብኝት ጋዜጠኛው ኄኖክ ሥዩም ይናገራል፡፡
በዚኽ ሐሳብ የሚስማሙት፣ የኢትዮጵያ ቱሪዝም እና ሆቴል ማርኬቲንግ ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታሁን ዓለሙ ደግሞ፣ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ፣ ሰላም ያለባቸውን አካባቢዎች በማስተዋወቅ በተሠራው ሥራ መሻሻሎች እንደታዩ ይገልጻሉ፡፡
በጉዳዩ ላይ፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሓላፊዎችን አስተያየት ለማካተት ያደረግነው ጥረት ባይሳካም፣ ሚኒስትሯ ናሲሴ ጫሊ፣ በ2016 ሩብ ዓመት፣ “የዓለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ የቱሪስት ፍሰት ጨምሯል፤” ሲሉ፣ ለመንግሥት ብዙኀን መገናኛዎች ተናግረዋል፡፡