በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ አንዲት ከተማን ሲቆጣጠር በሺሕ የሚቆጠሩ ጥለው ወጡ


የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ አዛዥ ጄነራል አምዳን ዳጋሎ (ፎቶ ፋይል፣ ሮይተርስ)
የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ አዛዥ ጄነራል አምዳን ዳጋሎ (ፎቶ ፋይል፣ ሮይተርስ)

ከሱዳን ሠራዊት ጋር በመፋለም ላይ ያሉት የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች፣ ዋድ ማዳኒ የተባለች ከተማን ትናንት ሲቆጣጠሩ፣ በከተማዋ በሚገኘው የዕርዳታ ማከፋፈያ ሰፈር የነበሩ በሺሕ የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ለመሸሽ ተገደዋል፣።

ከተማዋ በሱዳን ከሚገኙ ደህንነታቸው አስተማማኝ ከነበሩ ጥቂት ቦታዎች አንዷ እንደነበረች በሱዳን የኖርዌይ ፍልሰተኞች ም/ቤት ሃላፊ ዊሊያም ካርተርን ጠቅሶ ኤኤፍፒ ዘግቧል።

180 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው በመዲናዋ ካርቱም እንደነበረው ከባድ ውጊያ፣ በዋድ ማዳኒ ከተማም ተዋጊ ጄቶች በአየር ሲበሩ እና በየቦታው ከባድ ፍንዳታ ሲሰማ ውሏል። የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በከተማዋ ምሥራቅ በኩል የጦር ሰፈሩን ምሥርቷል ተብሏል።

ኃይሉ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ ተፈናቃዮች ወደሚገኙባት አል ጃዚራ ግዛት ከመግባት እንዲቆጠብና መዲናዋ ዋድ ማዳኒ ላይ ጥቃት እንዳይሰነዝር የአሜሪካው አምባሳደር ጃን ጋድፍሬይ ጥሪ አቅርበዋል።

የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ግስጋሴውን የሚቀጥል ከሆነ፣ ሲሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚደርስና የሰብዓዊ ሥራውም እንደሚስተጓጎል አምባሳደሩ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

በከተማዋ ከሚገኙ 700ሺሕ ነዋሪዎች ውስጥ፣ 270 ሺሕ የሚሆኑት በዕርዳታ ላይ ጥገኛ እንደሆኑ ተመድ አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG