በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻድ በአዲስ ሕገ-መንግስት ላይ የሕዝበ ውሳኔ ድምፅ ሰጠች


የቻድ ጠቅላይ ሚንስትር ሳለህ ኬብዛቡ ድምፅ ሲሰጡ (ፎቶ ኤኤፍፒ፣ ታህሳስ 17፣ 2023)
የቻድ ጠቅላይ ሚንስትር ሳለህ ኬብዛቡ ድምፅ ሲሰጡ (ፎቶ ኤኤፍፒ፣ ታህሳስ 17፣ 2023)

ቻዳዊያን በአዲስ ሕገ-መንግስት ላይ ዛሬ የሕዝበ ውሳኔ ድምፅ ሲሰጡ ውለዋል። ወደ ምርጫ የሚደረገው ጎዞ የሚጀመርበት እና ቃል ወደተገባው የሲቪል አስተዳደር አገሪቱ የምትመለስበት ሂደት ነው ተብሏል።

አብዛኛዎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና የሲቪል ማኅበረሰቡ ግን ሕዝቡ ድምፅ እንዳይሰጥ አድማ ጠርተዋል። ምክንያታቸውም፣ ድምፅ አሰጣጡ የተመቻቸው አሁን የሽግግር ፕሬዝደንት የሆኑትን ጄኔራል ማሃማት ኢድሪስ ዴቢ ኢትኖ መልሶ ወደ ስልጣን ለማምጣት ነው የሚል ነው። ከ 33 ዓመታት በፊት በአባታችው የተጀመረውን የቤተሰብ ሥልጣን ለማስቀጠል ያለመ ነው ባይ ናቸው።

በገዢው ሁንታ የሚመራው እና ሕገ-መንግስቱ እንዲፀድቅ የሚንቀሳቀስው ቡድን፣ በገንዘብ በመደገፍ፣ ከፍተኛ ዘመቻ አድርጓል ተብሏል። ቀድሞውንም የተከፋፈለው የተቃዋሚው ጎራ መሪዎች፣ ላለፈው አንድ ዓመት እስር፣ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ገጥሟቸዋል።

ኢድሪስ ዴቢ በመዲናዋ ኢንሜጀና ድምፅ በመስጠት ቀዳሚ ሆነዋል። ውጤቱ ሳምንት እሁድ ይፋ እንደሚሆን የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG