በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮንጎው ተቃዋሚ፣ ከአማጺው ኤም 23 ጋር እንደሚተባበሩ አስታወቁ


ኮርኔሊ ናንጋ (ፎቶ ፋይል፣ ኤኤፍፒ))
ኮርኔሊ ናንጋ (ፎቶ ፋይል፣ ኤኤፍፒ))

በኬንያ በስደት የሚኖሩ የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ተቃዋሚ ቡድን መሪ፣ ከአማጺው ኤም23 ጋር የፖለቲካና ወታደራዊ ትብብር እንደሚያደርጉ ማስታውቃቸውን ተከትሉ፣ ኪንሻሳ የኬንያውን አምባሳደር ለጥያቄ ጠርታለች፡፡

ኮንጎ በመጪው ሳምንት ምርጫ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ስትሆን፣ በልኬንያ በጥገኝነት የሚኖሩት የተቃዋሚው መሪ፣ ከአማጺው ቡድን ጋር ማበራቸውን ማስታወቃቸው ውጥረትን ፈጥሯል።

የተቃዋሚው መሪ እና የቀድሞው የኮንጎ ምርጫ ኮሚሽን ኃላፊ የነበሩት ኮርኔሊ ናንጋ፣ በናይሮቢ በሚገኝ አንድ ሆቴል፣ ከኤም23 ጋር እንደሚቆሙ፣ የአማጺው “ፕሬዝደንት” ተደርገው ከሚታዩት በርትራንድ ቢስሟ ጋር በመሆን አስታውቀዋል።

ድርጊቱ ናይሮቢን ዲፕሎማሲያዊ ዋጋ ያስከፍላታል ስትል ኪንሻሳ ዝታለች፡፡

ትናት ዓርብ ማምሻውን ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የኮንጎው የማስታወቂያ ሚኒስትር ፓትሪክ ሙያያ፣ ከኬንያ ማብራሪያ እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG