በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዙማ በመጪው ምርጫ ለኤኤንሲ ድምፃቸውን እንደማይሰጡ አስታወቁ


 ጄከብ ዙማ (ፎቶ ፋይል፣ ኤኤፍፒ)
ጄከብ ዙማ (ፎቶ ፋይል፣ ኤኤፍፒ)

የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት ጄከብ ዙማ፣ በአንድ ወቅት እርሳቸውም ይመሩት ለነበርው ገዢው ፓርቲ ኤኤንሲ በመጪው ምርጫ ድምፃቸውን እንደማይሰጡ አስታውቀዋል።

በሙስና ቅሌት ከስልጣን ተወግደው በሰሪል ራማፎሳ የተተኩት ዙማ፣ የ15 ወራት እስር ተፈርዶባቸው፣ በጤና ምክንያት በሚል ከሁለት ወር እስር በኋላ ምሕረት ተደርጎላቸው ነበር። ዙማ፤በሰሪል ራማፎሳ ለሚመራው ኤኤንሲ ድምፃቸውን እንደማየጡ አስታውቀው፤ ድምፃቸውን በቀድሞ የኤኤንሲ ወታደራዊ ክንፍ ለተሰየመ አዲስ ፓርቲ እንደሚሰጡ ተናገረዋል።

“የዲሞክራሲ መዋቅሮች ፈርሰዋል፣ ገንዘብም ምርጫን ለመወሰን ጥቅም ላይ ውሏል” የሚሉት ዙማ፣ “ኤኤንሲ በሚሰጠው ውሳኔዎችም ውስጥ ማጭበርበር አለ” ሲሉ ይከሳሉ።

ከ1994 ወዲህ ለመጀመሪያ ግዜ ኤኤንሲ በምርጫ እንደሚሸነፍ ዙማ ተንብየዋል።

አጨቃጫቂው ዙማ በፓርቲው ውስጥ አሁንም ተጽእኖ እንዳላቸውና ጠንካራ ደጋፊዎች እንዳሏቸውም ይነገራል። ለእስር በተዳረጉበት ወቅት በተነሳ ተቃውሞ፣ 350 የሚሆኑ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG