በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሁቲ አማጺያን በቀይ ባሕር ላይ የሚያደርሱት ጥቃት ጨምሯል


የሁቲ ሄሊኮፕተር፣ እቃ ጫኝ መርከብ ላይ ሲያንዣንብብ (ፎቶ ፋይል፣ ሮይተርስ)
የሁቲ ሄሊኮፕተር፣ እቃ ጫኝ መርከብ ላይ ሲያንዣንብብ (ፎቶ ፋይል፣ ሮይተርስ)

የየመን ሁቲ አማጺያን በቀይ ባህር በኩል በሚተላለፉ መርከቦች ላይ የሚያደርሱት ጥቃት በመጨመር ላይ ነው ተብሏል።

የእስራኤል እና ሐማስ ጦርነት ከጀመረ ወዲህ እየተባባሰ በመጣው ጥቃት፣ በጦርነቱ መጀመሪያ አካባቢ ኢላማ የነበሩት ከእስራኤል ጋር ግንኙነት ያላቸው መርከቦች ሲሆኑ፣ በአሁኑ ወቅት ግን ሌሎችም ከእስራኤል ጋር ግንኙነት የሌላቸው መርከቦች ኢላማ በመደረግ ላይ ናቸው ተብሏል።

ታላላቅ የመርከብ ኩባንያዎች፣ ሌላ መመሪያ እስሚሰጥ ድረስ፣ መርከቦቻቸው ባሉበት የባሕር ላይ ኬላዎች እንዲቆሙ አዘዋል።

በዓለም ንግድ ትልቅ የደም ሥር ከሆኑት አንዱ ተደርጎ በሚታየው ቀይ ባሕር ላይ የሚፈጸመው ጥቃት፣ የነዳጅ፣ እህል እና ሌሎችም ቁሶች ዝውውርን ስለሚገታ ቀውስ እንዳይስከትል ተሰግቷል።

ከጦርነቱ መፈንዳት ወዲህ፣ በኢራን የሚደገፉ ቡድኖች በመካከለኛው ምሥራቅ በሚገኙ የአሜሪካ መከላከያ አባላት ላይ የሚያደርጉትን ጥቃት በከፍተኛ መጠን እንደጨመሩም ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG