በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል “በስህተት” ሶስት ታጋቾችን ገድያለሁ አለች


እስራኤላዊ ታጋቾቾ መገደላቸው ከተሰማ በኋላ፣ በቴል አቪቭ የተካሄደ የተቃውሞ ሰልፍ (ፎቶ ሮይተርስ ታህሳስ 15፣ 2023)
እስራኤላዊ ታጋቾቾ መገደላቸው ከተሰማ በኋላ፣ በቴል አቪቭ የተካሄደ የተቃውሞ ሰልፍ (ፎቶ ሮይተርስ ታህሳስ 15፣ 2023)

በሰሜን ጋዛ በሐማስ ላይ ባደረሰችው ጥቃት ሶስት ታጋቾችን “በስህተት” እንደገደለች እስራኤል አስታውቃለች።

በሐማስ ተይዘው የነበሩት ሶስቱ እስራኤላዊያን ታጋቾች የተገደሉት ትናንት ዓርብ ሲሆን፣ ትጋቾቹ ምናልባትም ሐማስ ትቷቸው የሄደ ወይም ከእገታው ለማምለጥ ሲሞክሩ የነበሩ ሊሆኑ ይችላሉ ሲል የእስራኤል መከላከያ ኃይል አስታውቋል።

ከ130 በላይ የሚሆኑ ታጋቾች አሁንም በሐማስ እጅ እንደሚገኙ ተነግሯል።

18ሺሕ ፍልስጤማውያን ያለቁበትን ጦርነት፣ እስራኤል ከፍተኛና ሰፊ የጥቃት ዘመቻ ከማድረግ ይልቅ፣ ውስን የሆኑ ኢላማዎች ላይ ብቻ እንድታተኩር አንድ ከፍተኛ የባይደን አስተዳደር ባለሥልጣን እስራኤልን መጠየቃቸው ታውቋል።

ትናንት ዓርብ አንድ የአል ጃዚራ ቴሌቪዥን የካሜራ ባለሙያ በእስራኤል ጥቃት መገደሉ ታውቋል። አል ጃዚራ እንዳለው፣ የካሜራ ባለሙያው ሳመር አቡዳቃ ከተመታ በኋላ፣ የሕክምና ቡድኖች ለመርዳት ሙከራ ቢያደርጉም በእስራኤል ኃይሎች መከልከልከላቸው ታውቋል።

ጦርነቱ በፍልስጤማውያን ሲቪሎች ላይ ከፍተኛ ስቃይ ባስከተለበት በዚህ ወቅት፣ እስራኤል ከፍተኛና ሰፊ የጥቃት ዘመቻ ከማድረግ ይልቅ፣ ውስን የሆኑ ኢላማዎች ላይ ብቻ እንድታተኩር አሜሪካ ጥሪ በማድረግ ላይ ነች፡፡

የአሜሪካ ብሔራዊ ፀጥታ አማካሪ ጄክ ሰለቨን ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ነታንያሁ እና ከመከላከያ ሚኒስትሩ ዮአቭ ጋላንት ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸውና፣ እስራኤል የጥቃት ዘመቻዋን በምትቀንስነት ጉዳይ ላይ መምከራቸውን የብሔራዊ ፀጥታ ም/ቤቱ አስተባባሪ ጃን ኪርቢ ዋሽንግተን ላይ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG