በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጥንታዊት ኢትዮጵያን ከዘመነኛው ያገናኘው የዋልተርስ አርት ሙዚየም የቅርስ እና የጥበብ ዐውደ ርእይ


ጥንታዊት ኢትዮጵያን ከዘመነኛው ያገናኘው የዋልተርስ አርት ሙዚየም የቅርስ እና የጥበብ ዐውደ ርእይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:09 0:00

ጥንታዊት ኢትዮጵያን ከዘመነኛው ያገናኘው የዋልተርስ አርት ሙዚየም የቅርስ እና የጥበብ ዐውደ ርእይ

በዩናይትድ ስቴትስ ሜሪላንድ ግዛት ቦልቲሞር ከተማ የሚገኘው አንጋፋው የዋልተርስ አርት ሙዚየም፣ ከ30 ዓመታት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ፣ ከመላ ዩናይትድ ስቴትስ ግዙፍ የተባለውን፥ የኢትዮጵያ ጥንታዊ፣ ዓለማዊ እና መንፈሳዊ ቅርሶችን ስብስብ፣ ለሦስት ወር እይታ ይፋ አድርጓል።

ዓለም አቀፍ ታሪካዊ እና ሥነ ጥበባዊ ሥራዎችን የሚይዘው ሙዚየሙ፣ ከጥንታውያን ስብስቦች በተጨማሪ፣ የዘመነኛ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶችን እንደ እስክንድር ቦጎስያን፣ ኤሊያስ ስሜ፣ ወሰን ወርቅ ኪርሶፍ፣ ቲዮ እሸቱ እና ጸደይ መኰንን የመሰሉ፣ የዘመናዊት ኢትዮጵያንና የአኹነኛ ጥበብ አንጋፋ ባለሞያዎችን ሥራዎችንም አካቶ ይዟል።

በተመሳሳይ ዋሽንግተን ዲሲ ተወልዳ ያደገችው ዓለም አቀፍ የጥበብ ባለሞያ እና ተመራማሪ ጸደይ መኰንን፣ የዐውደ ርእዩ ተጋባዥ እና አጋር አዘጋጅ ስትኾን፤ በተጨማሪም ‘ሠናይት እና ናሆም’ የተሰኘውን በመስተዋት የተጌጠ ኢንስቶልመንት አርት የቅርጽ ሥራዋን አቅርባለች።

ኤደን ገረመው፣ በኢትዮጵያ መንፈሳዊ ሥዕሎች ላይ፣ ከ30 ዓመታት በላይ ምርምር ያደረገችውን ክርስቲን ሻካን፣ ዓለም አቀፍ የጥበብ ባለሞያን ጸደይ መኰንንና ሌሎችንም ባለሞያዎችን አነጋግራ ያሰናዳችው ዘገባ ቀጥሎ ይቀርባል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG