በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍልስጥዔማዊያን እስራኤል ራፋ ላይ ባደረሰችው ጥቃት የቆሰሉ ሰዎችን ለማትረፍ እየተሯሯጡ ናቸው


የፍልስጤማውያን ሰፈራ
የፍልስጤማውያን ሰፈራ

እስራኤል በማዕከላዊ ኻን ዮኑስ የመኖሪያ አካባቢዎች ዛሬ ሐሙስ ባደረሰችው የአየር ጥቃት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ ፍልስጥዔማውያን በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች አስከሬኖችን እና ቁስለኞችን ለማንሳት እየተጣደፉ ናቸው፡፡

ከሁለት ሳምንታት በፊት የተኩስ አቁም ስምምነቱ መፍረሱን ተከትሎ ጦርነቱ ተባብሶ በመላው የጋዛ ሰርጥ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም በሰው እና በንብረት ላይ እጅግ የከበደ አደጋ እንደሚከተል አስጠንቅቀዋል።

እስራኤል ወታደራዊ ዘመቻዋን የጀመረችው ጋዛን የሚያስተዳደረው ሃማስ እ.ኤ.አ ጥቅምት 7 ድንበር ተሻግሮ ባደረሰው ጥቃት 1,200 እስራኤላውያንን ገድሎ እና 240 ማገቱን ተከትሎ ነው፡፡ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የእስራኤል ወታደሮች ጋዛን ከብበው አብዛኛውን አወድመዋል፡፡

በፍልስጤም የጤና ባለስልጣናት ወደ 19,000 የሚጠጉ ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል፡፡ ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ በየፍርስራሹ ውስጥ ተቀብረዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG