በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ኅብረት 61ሺሕ ፍልሰተኞችን ተቀብሎ እንደሚያሰፍር አስታወቀ


በጂኒቫ እየተካሔደ ባለው የተመድ ዓለም አቀፍ የፍልሰት ጉባኤ
በጂኒቫ እየተካሔደ ባለው የተመድ ዓለም አቀፍ የፍልሰት ጉባኤ

የአውሮፓ ኅብረት በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት፣ 61 ሺሕ ፍልሰተኞችን በአባል አገራቱ ለማስፈር እንደሚሠራ አስታውቋል።

የአውሮፓ ኅብረት፤ እ.አ.አ ከ2015 ጀምሮ 175ሺሕ ፍልሰተኞችን እንዳሰፈረ፣ የኅብረቱ የውስጥ ጉዳይ ኮሚሽነር ይልቫ ጆሃንሰን በጂኒቫ እየተካሔደ ባለው የተመድ ዓለም አቀፍ የፍልሰት ጉባኤ ጎን ለጎን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

14 የኅብረቱ አባል ሀገራት፣ በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት 61ሺሕ ፍልሰተኞችን ለማስፈር ቃል እንደገቡ፣ ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል። ከእነርሱም፣ 31 ሺሕ የሚደርሱቱ፣ በተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር በኩል በሚፈጸም ፕሮግራም እንደሚሰፍሩ ጨምረው ገልጸዋል። የፍልሰተኞቹ ቁጥር፣ ከዚኽ ቀደም ከነበረውም ከፍ ያለ እንደኾነ ታውቋል።

በተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር በኩል የሚካሔደው ሰፈራ፣ ለፍልሰተኞች ከለላ እና ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ለመስጠት ፈቃደኛ ወደኾነ ሦስተኛ አገር ተዛውረው እንዲኖሩ የሚያስችል ነው።

የአውሮፓ ኅብረት፣ ባለፉት ሦስት ዓመታት፣ አንድ ሚሊዮን ለሚኾኑ ሰዎች ከለላ እንደሰጠና እኒኽም፣ በዓለም ዙሪያ ካሉት ፍልሰተኞች ውስጥ 20 በመቶ እንደኾኑ ተመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG