በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስለ ሰብአዊ መብቶች ለማስገንዘብ ባለመው የዘንድሮ የፊልም ፌስቲቫል ውጤት እያየበት እንደኾነ ኮሚሽኑ ገለጸ


ስለ ሰብአዊ መብቶች ለማስገንዘብ ባለመው የዘንድሮ የፊልም ፌስቲቫል ውጤት እያየበት እንደኾነ ኮሚሽኑ ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:36 0:00

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ በየዓመቱ የሚያዘጋጀው የፊልም ዐውደ ትርኢት /ፌስቲቫል/፣ዘንድሮ ለሦስተኛ ጊዜ፣ በዚኽ ሳምንት ተጀምሯል፡፡

ከትላንት በስቲያ ሰኞ፣ ታኅሣሥ 1 ቀን 2016 ዓ.ም. በዐዲስ አበባ የተጀመረው ሦስተኛው ዙር የፊልም ዐውደ ትርኢት፣ የአጫጭር ፊልም እና የፎቶግራፍ ውድድሮችን ጨምሮ፣ ከ160 በላይ የኪነ ጥበብ ሥራዎችን ያካተተ ነው።

በባለሞያዎች ከተዘጋጁት ፊልሞች መካከል፣ የአሕመድ አብዱ ሰዒድ፣ “ለምን” የተሰኘ አጭር ፊልም አሸናፊ ኾኗል፡፡ በጀማሪ ባለሞያዎች ከተሠሩት መሀከል ደግሞ፣ የዐዲሱ ደመቀ ‘‘ስለ ሕይወት’’ ፊልም አሸንፏል፡፡

የዘንድሮው፣ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል፣ በኮሚሽኑ፣ “አሳሳቢ” ተብለው በተለዩት በሕይወት የመኖር እና የመኖሪያ ቤት የማግኘት መብቶች ላይ ትኩረት አድርጓል፡፡

ስለ ፌስቲቫሉ አስተያየት የሰጡት፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶር. ዳንኤል በቀለ፣ የፌስቲቫሉ ዓላማ፥ ኪነ ጥበብን በመጠቀም፣ ስለ ሰብአዊ መብቶች ግንዛቤ ለመፍጠር እንደኾነ ገልጸው፣ አካሔዱን ውጤት እያየንበት ነው፤ ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG