በጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሥልጣናቸው ተነሥተው ከትላንት በስቲያ ምሽት በቁጥጥር ሥር የዋሉት የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ደ’ኤታ አቶ ታየ ደንዳአ፣ ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ፣ ባለቤታቸው ተናገሩ።
የፌደራል የጸጥታ ኀይሎች፣ አቶ ታየን በቁጥጥር ሥር ካዋሉ በኋላ፣ በዐዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው የፌደራል ወንጀል ምርመራ እንደሚገኙ፣ ባለቤታቸው ወይዘሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። ባለቤታቸው ተጠርጥረው ስለታሰሩበት ምክንያት የሚገልጽላቸው አካል እንዳላገኙም አመልክተዋል።
ስለ አቶ ታዬ እስር፣ ከኢትዮጵያ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።