በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በወለጋ ዞኖች የጸጥታ ችግር የደረሰ የቡና ምርት ለመሰብሰብ እንደተቸገሩ አርሶ አደሮች ገለጹ


በወለጋ ዞኖች የጸጥታ ችግር የደረሰ የቡና ምርት ለመሰብሰብ እንደተቸገሩ አርሶ አደሮች ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:58 0:00

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች የጸጥታ ችግር ምክንያት፣ የደረሰ የቡና ምርታቸውን መሰብሰብ እንዳልቻሉ፣ ነዋሪዎች ገለጹ።

የሁለቱ ዞኖች ልዩ ልዩ ወረዳዎች ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለጹት፣ በመንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል በሚደረገው ውጊያ፣ በቡና ማሳዎቻቸው ተገኝተው ምርታቸውን እንዳይሰበስቡ በጸጥታ ኀይሎች ተከልክለዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ደግሞ፣ በኹሉም የክልሉ ቡና አብቃይ አካባቢዎች ላይ፣ ምርቱ በተመሳሳይ መልኩ እየተሰበሰበ ነው፤ ሲል አስታውቋል።

የጸጥታው ችግር፣ በቡና ምርት ስብሰባ ላይ ያሳደረውን ጫናና የነዋሪዎቹን አቤቱታ አስመልክቶ፣ ከቡና እና ሻይ ባለሥልጣን፣ ከኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ማስፋፊያ ኤጀንሲ፣ ከኦሮሚያ ቡና ዩንዬንና ከክልሉ የጸጥታ ቢሮ ምላሽ እና አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG