በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግብፅ ድምፅ እየሰጠች ነው


ፎቶ ሮይተርስ (ታህሳስ 10፣ 2023)
ፎቶ ሮይተርስ (ታህሳስ 10፣ 2023)

ግብፃውያን ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ ፕሬዝደንታቸውን ለመምረጥ ድምፅ ሲስጡ ውለዋል። ምርጫው በጋዛ የሚካሄደው ጦርነት ጥላውን ያጠላበት እንደሆነ ሲነገር፣ በሥልጣን ላይ ያሉት አብደል ፈታህ አል ሲሲ ለሶስተኛ ግዜ ደግመው እንደሚመረጡ ብዙም የሚጠራጠር የለም ተብሏል።

በታሪኳ በከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ በተመታችው ግብጽ፣ የዋጋ ግሽበቱ 40 በመቶ የደረሰ ሲሆን፣ ገንዘቧ ግማሽ ዋጋውን በማጣቱ፣ ከውጪ የምታስገባው ምርት ዋጋ አሻቅቧል።

በዚህ ምርጫ ኢኮኖሚው ዋና ጉዳይ ነው ተብሏል።

ከኢኮኖሚ ቀውሱ በፊትም ቢሆንም፣ 106 ሚሊዮን ከሚሆነው ሕዝብ፣ ከሶስት እጅ ሁለቱ ከድህነት ወለል በታች እንደሚኖር ታውቋል።

የምርጫ ጣቢያዎች ጠዋት ሶስት ሰዓት ላይ ከመከፈታቸው በፊት ሰዎች በብዛት ሰልፍ ይዘው የታዩ ሲሆን፣ ድምፅ መስጠቱ እስከ ማክሰኞ ሲቀጥል፣ የምርጫው ውጤት የነገ ሳምንት ሰኞ ይፋ ይሆናል ተብሏል።

በግብፅ ታዋቂ የሆኑት ሁለት ተቃዋሚዎች ለመወዳደር ሞክረው የነበረ ቢሆንም፣ ወዲያውኑ እንዲገለሉ ተደርጓል። አንደኛው በእስር ቤት ሲገኙ፣ ሌላው ደግሞ የፍርድ ሂደት ላይ እንደሆኑ ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG