የምዕራብ አፍሪካ አገራት መሪዎች በቀጠናው በተባባሰው ቀውስ ላይ ለመነጋገር አቡጃ ናይጄሪያ ውስጥ ስብሰባ ተቀምጠዋል።
ባለፉት ሶስት ዓመታት በአራት አገራት፣ ማለትም ማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ጊኒ እና ኒዤር መፈንቅለ መንግስት ያስተናገደው ቀጠና፣ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ (ኤኮዋስ) አባል አገራት ከሆኑት ውስጥ፣ ሴራ ሊዮን እና ጊኒ ቢሳዎም ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ መፈንቅለ መንግስት ተሞክሮባቸዋል።
እያደገ የመጣ የሳህል ጂሃዲስቶች ስጋት ባለበት ቀጠና፣ የፈረንሣይ ጦር ለቆ በመውጣቱ፣ ቀውሱ ወደ ደቡብ አገራት ማለትም ወደ ጋና፣ ቶጎ፣ ቤኒን እና አይቮሪ ኮስት እንዳይስፋፋ ተሰግቷል።
በኒዤር ባለፈው ሐምሌ የተካሄደው መፈንቅለ መንግስት ዓለም አቀፍ ትኩረት የሳበ ሲሆን፣ ኤኮዋስ ከበድ ያለ ማዕቀብ ጥሎ ከአገሪቱ ጋር የሚካሄድ ንግድ እንዲቋረጥ አድርጓል።
ከሳህል ነውጠኞች ጋር በሚደረገው ፍልምያ የምዕራቡ ዓለም አጋር የሆነችው ኒዤር፣ የፈረንሳይ ጦር ለቆ እንዲወጣ ያደርገች ሲሆን፣ አሜሪካ ግን አሁንም የጦር ዓባላቷ በአገሪቱ እነደሚገኙ ተነግሯል።
የአቡጃው የኤኮዋስ ስብሰባ፣ በስደት ላይ ያሉትን የኒዤር ጠቅላይ ሚኒስትር የጋበዘ ሲሆን፣ በአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ሓላፊ ሞሊ ፊ፣ ኔዤር ወደ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር የምትመለስበትን እና ለሳህል ጸጥታ የሚሰጥን ድጋፍ በተመለከተ ለመነጋገር በስብሰባው እንደተገኙም ታውቋል።
መድረክ / ፎረም