በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አውሮፓ የሰው ሰራሽ ልህቀት መመሪያን ለማጽደቅ ስምምነት ላይ ደረሰች


ሰው ሰራሽ ልህቀት
ሰው ሰራሽ ልህቀት

የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ተደራዳሪዎች ትላንት አርብ ቴክኖሎጂ በተለይም እንደ ቻት ጂፒቲ እና የሰዎችን መልክ በመለየት የሚሰሩ፣ የሰው ልጅ ህይወትን የሚያቀሉ፤ ነገር ግን አጠቃላይ ህልውናው ላይ ስጋት የደቀኑ፤ የሰው ሰራሽ ልህቀቶችን በተመለከተ፤ የህግ ማዕቀፍ እንዲወጣ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽነት ቴሪ ብሬንተን ትላንት እኩለ ሌሊት ላይ “ስምምነት” ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ ያሰፈሩ ሲሆን “አውሮፓ በሰው ሰራሽ ልህቀት ላይ ግልጽ የሆነ መመሪያዎች ያሏት የመጀመሪያዋ አህጉር ሆናለች” ሲሉ አክለዋል።

እንደ ‘ኦፕን ኤ አይ’ እና ‘ቻት ጂ ፒቲ’ ያሉ የሰው ሰራሽ ልህቀት ስርዓቶች በአለም ላይ እጅግ እየበዙ የመጡ ሲሆን የግለሰቦችን ጽሑፎችን፣ ፎቶዎችን እና ዘፈኖችን በጥራት አስመስለው የማዘጋጀት ችሎታ አላቸው። ነገር ግን በፍጥነት በማደግ ላይ ያለው ቴክኖሎጂ በስራ፣ በግላዊነት እና በቅጂ መብት ጥበቃ እና በራሱ በሰው ልጅ አኗኗር እና ህይወት ላይ ሊያስከትለው የሚችለው አደጋ የተነሳ ስጋት ተፈጥሯል።

በተመሳሳይ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ብሪታኒያ፣ ቻይና እና የቡድን ሰባት ህብረት እና ዴሞክራሲያዊ ሀገራት የአውሮፓን ኣርአያ በመከተል ሰው ሰራሽ ልህቀትን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ሰነዶችን በማዘጋጀት ላይ ይገኛሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG