በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻይናው ፕሬዘዳንት ቪየትናምን ሊጎበኙ ነው


የቪየትናም ጠቅላይ ሚኒስትር እና የቻይናው ፕሬዘዳንት (ከግራ ወደ ቀኝ)
የቪየትናም ጠቅላይ ሚኒስትር እና የቻይናው ፕሬዘዳንት (ከግራ ወደ ቀኝ)

የቻይናው ፕሬዘዳንት ሺ ጂን ፒንግ ከስደስት ዓመታት ጸብ በኋላ በቀጣይ ሳምንት ለሥስተኛ ጊዜ ወደ ቪየትናም እንደሚጓዙ ተገልጿል። የፕሬዘዳንቱ ጉብኝት አሜሪካ ከቪየትናም ጋር ያላትን ግንኙነት እያፋፋመች ባለችበት ወቅት የሚደረግ ነው።

ፕሬዘዳንቱ የፊታችን ማክሰኞ እና ረቡዕ በቪየትናም የሚቆዩ ሲሆን፤ ጉብኝታቸው በኮሚኒስት አንድ ፓርቲ ብቻ የሚመሩ ሀገራት “አጠቃላይ ስልታዊ አንድነታቸውን” ለ15ኛ ጊዜ ከሚያከብሩበት ክብረ በዓል ጋር የገጠመ ነው።

ይህ ጉብኝት ቪየትናም ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የጋራ ትብብር ለማድረግ ከተፈራረመችበት እና እራሳቸው ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ከሄዱበት፤ ከመስከረሙ የቪየትናም ጉብኝት በኋላ የተደረገ መሆኑ አሜሪካ ከቪየትናም ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከቻይና ጋር የሚያስተካከል ሆኗል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG