በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዋይት ሃውስ ለእስራኤል የታንክ ተወንጫፊዎችን ለመላክ የኮንግረስን ፍቃድ እየጠየቀ ነው


ታንክ 2023
ታንክ 2023

የፕሬዘዳንት ባይደን አስተዳደር የዩናይትድ ስቴትስ ኮንግረስ እስራኤል በሀማስ ላይ የምትጠቀማቸው ታንኮች የሚውሉ 45 ሺህ ተወንጫፊ መሳሪያዎች ዩናይትድ ስቴትስ እንድትፈቅድ በጠየቁበት ማግስት እስራኤል ሌሊቱን ጋዛን ስትደበድብ ማደሯን የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ ባለስልጣን አስታወቁ።

ይህ ጥቃት የተከተለውም ዩናይትስ ስቴትስ ድምጽን በድምጽ የመሻር የቪቶ መብቷን በመጠቀም አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዳይደረግ በከለከችበት ማግስት ነው።

በሌላ በኩል የአለም ጤና ድርጅት ስራ አስፈፃሚ ቦርድ በጋዛ የጤና ሁኔታ ላይ ለመወያየት ነገ እሁድ ሊገናኝ ቀጠሮ ይዟል። ከ 10 በላይ የዓለም ጤና ድርጅት አባል ሀገራት በጋዛ ስላለው አስከፊው የሰብአዊ ሁኔታ “ከባድ ስጋት” እንዳላቸው አስታውቀዋል።

የመሳሪያ ሽያጩ ከ500 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚያውጣ ሲሆን ኢመደበኛ በሆነ ሁኔታ በሴኔት የውጭ ጉዳይ ግንኙነት እና በውጭ ጉዳይ ኮሚቴዎች እየታየ ነው። ይኸም የፕሬዘዳንት ጆ ባይደን መንግስት ለዩክሬን ከሚያደርጉት ድጋፍ ጋር ሲዳበል 110.5 ቢሊየን ዶላር እንደሚደርስ ተገልጿል።

ማንነታቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት ጉዳዩን እንደነገሯቸው የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ቃል አቀባይ ጆሽ ፖል ለሮይተር የዜና አውታር አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG