በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩስያ የአፍሪካ ቀንድ ተጽእኖ እየጨመረ እንደኾነ ምሁራን ገለጹ


የሩስያ የአፍሪካ ቀንድ ተጽእኖ እየጨመረ እንደኾነ ምሁራን ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:25 0:00

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፣ ሩሲያ በአፍሪካ ሀገራት ውስጣዊ ጉዳዮች ያላት ተጽእኖ እየጨመረ እንደኾነ፣ የሰላም እና ደኅንነት ባለሞያው አቶ በቃሉ ዋቺሶ ይናገራሉ፡፡

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መምህር የኾኑት አቶ በቃሉ፣ በተራዘመው የዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ምክንያት የተፈጠረው ኢኮኖሚያዊ ተጽእኖ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ውስጣዊ አለመረጋጋት አስተዋፅኦ እንዳደረገ ገልጸዋል፡፡

በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የፖለቲካ ሳይንስ ዋና ተመራማሪው ዶክተር ዳር እስከ ዳር ታየ በበኩላቸው፣ ሩሲያ፣ በአፍሪካ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ካላቸው ናይጀርያ እና ኢትዮጵያ ጋራ ጠንካራ ግንኙነት እንዳላት ይናገራሉ፡፡

ሩሲያ፣ በቀይ ባሕር ፖለቲካ ውስጥ ለመሳተፍ ካላት ፍላጎት የተነሳም፣ በሱዳንና በሶማሌ ላንድ የጦር ሰፈሮችን ለመመሥረት እንቅስቃሴ ጀምራ እንደነበርም፣ ዶር. ዳር እስከ ዳር ገልጸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG