የዩናይትድ ስቴትስ ነባር አሜሪካውያን ማኅበረሰቦችን አስመልክቶ፣ “ዐዲስ እና የተሻለ የታሪክ ምዕራፍ” ለማስመዝገብ ቁርጠኛ እንደኾኑ፣ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስታወቁ፡፡
ፕሬዚዳንቱ፣ ከትላንት በስቲያ ረቡዕ እንዳስታወቁት፣ አስተዳደራቸው፣ ከ570 ለሚበልጡ ነባር አሜሪካውያን ማኅበረሰቦች፣ ከፌዴራል መንግሥት ገንዘብ በመመደብ ለመደገፍ ወስኗል፡፡
ከታላላቅ የነባሮቹ ማኅበረሰቦች የአንዱ መሪ፣ የአስተዳደሩን ጥረቶች አስመልክቶ ለቪኦኤ አስተያየታቸውን ሲሰጡ፣ በአገር በቀል ተወላጆች ታሪክ ውስጥ የተመዘገቡት አንዳንድ አድራጎቶች፣ ዛሬም ራቅ ባሉ የዓለም አካባቢዎች መከሠታቸውን ቀጥለዋል፤ ብለዋል፡፡
የቪኦኤዋ የኋይት ሐውስ ዘጋቢ አኒታ ፓወል፣ ከአገር አስተዳደር ሚኒስቴር ያጠናቀረችውን ሪፖርት፣ ቆንጅት ታየ ወደ ዐማርኛ መልሳዋለች፡፡