በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዐዲስ አበባ ከተማ ለእሑድ ከተጠራው ሰልፍ ጋራ በተያያዘ ብዙ ሰዎች እየታሰሩ ነው


ዐዲስ አበባ ከተማ ለእሑድ ከተጠራው ሰልፍ ጋራ በተያያዘ ብዙ ሰዎች እየታሰሩ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:30 0:00

በዐማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ የሚካሔደውን ጦርነት የተቃወሙ የፖሊቲካ ፓርቲዎች፣ ለነገ በስቲያ እሑድ ከጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ ጋራ በተያያዘ፣ የሰልፉ አስተባባሪዎች እንደታሰሩ፣ ኢሕአፓ አስታወቀ። ኢዜማ እና እናት ፓርቲዎችም፣ አባሎቻቸው እንደታሰሩ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡

የኢሕአፓ ፓርቲ ሊቀ መንበር ረዳት ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ፣ ታሳሪዎቹ ወደ አዋሽ አርባ እንደተወሰዱ ገልጸው፣ ለእሑድ የተጠራው ሰልፍ መሰረዙን እና ወደፊት እንደሚካሔድ አክለዋል፡፡

የመንግሥት የጸጥታ እና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኀይል በበኩሉ፣ ሰላማዊ ሰልፉን መነሻ በማድረግ ሽብር ለመፈጸም ዐቅደዋል፤ ያላቸውን 97 ተጠርጣሪዎች እንደያዘ፣ ትላንት ማምሻውን አስታውቋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG