በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አንጋፋውን የባህል ማዕከል ወደ ቀድሞ ዝናው የመመለስ የዩኒቨርሲቲው ውጥን ይሳካ ይኾን?


አንጋፋውን የባህል ማዕከል ወደ ቀድሞ ዝናው የመመለስ የዩኒቨርሲቲው ውጥን ይሳካ ይኾን?
please wait

No media source currently available

0:00 0:16:55 0:00

ግማሽ ምእት ዓመትን የተሻገረ ዕድሜ ያለው የዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል፣ ዐያሌ የኪነ ጥበብ ሰዎችን ያፈራ አንጋፋ ተቋም ነው፡፡

በቴያትር ሥራዎች፥ ያረፉት እነጸጋዬ ገብረ መድኅን፣ ወጋየሁ ንጋቱ፣ አባተ መኩርያን ጨምሮ፣ አኹንም ድረስ በሕይወት ያሉ ዝነኞች፣ ሥራዎቻቸውን ያሟሹበት ቤት ስለመኾኑ ይነገራል፡፡

በሙዚቃ፥ ዝነኛው የባህል ቡድን “ኦርኬስትራ ኢትዮጵያ” እና የሥነ ግጥም እንዲሁም የሥነ ጥበብ ሥራዎች በማዕከሉ ይቀርቡበት ነበር፡፡

በአሁኑ ወቅት፣ በፖለቲካዊ እና ሌሎችም ምክንያቶች፣ የመዘጋት ዕጣ ፈንታ የገጠሙት ማዕከሉ፣ ወደ ቀድሞ ስም እና ዝናው ለመመለስ ያስችላሉ፤ የተባሉ የኪነ ጥበብ ሥራዎች የሚመደረኩበት የጥበብ ፈለግ እና የጥበበኞች ዠማ ይኾን ዘንድ ጥረቶች ተጀምረዋል፡፡ ውጥኖቹ ይይዙለት ይኾን?

አስማማው አየነው፣ ይህን የምለሳ ጥረት መነሻ አድርጎ፣ የማዕከሉን ትዝታዎች ከዲሬክተሩ እና ከባለሞያዎቹ ጋራ ተጨዋውቶ ተከታዩን መሰናዶ አዘጋጅቷል፡፡

XS
SM
MD
LG