በተባበሩት አረብ ኢምሬትሷ ዱባይ እየተካሔደ ባለው የአየር ንብረት ጉባኤ፣ ለዓለም የከባቢ አየር ብክለት አንዱ መንሥኤ የኾነው የነዳጅ ዘይት ኢንዱስትሪዎች፣ “በርካታ ጉዳይ አስፈጻሚዎችን ጋብዘዋል” የሚል ክስ ቀርቦበታል፡፡
በጉባኤ ተሳታፊ የኾኑ የዓለም መሪዎች፣ እየጨመረ የመጣውን የከባቢ አየር ሙቀት መቆጣጠር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ሲከራከሩ ሰንብተዋል።
ሄንሪ ሪጅዌል ያጠናቀረውን የዚኽን ዘገባ ዝርዝር፣ አሉላ ወደ ዐማርኛ መልሶታል።